የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን እየሠራ መሆኑን ገለጸ

ሰኔ 3/2014 (ዋልታ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋናው አርጋ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የግብርና ዘርፉን ለመደገፍ እና ለማዘመን በርካታ ሥራ እየሠራ መሆኑን አስታወቁ፡፡

እንደ ሀገር የተያዘውን ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ግብ ከዳር ከማድረስ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በ2014 ዓ.ም ያመረታቸው የግብርና ማሽነሪዎች ላይ የጉብኝት መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋናው አርጋ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የግብርና ዘርፉን ለመደገፍ እና ለማዘመን በርካታ ሥራ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው እንደ ሀገር የተያዘውን ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ግብ ከዳር ከማድረስ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች መካከል የሆነው የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪም ለረጅም ዓመታት በአሠራር ችግር ምክንያት ወደ ሥራ ሳይገቡ የቆዩ ማሽነሪዎችን ወደ ገበያ እንዲቀላቀሉ እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል::

ኢንዱስትሪውም ከ277 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለበልግና መኸር የሚውሉ የግብርና ማሽነሪዎችን በማምረት ለተለያዩ የክልል ከተሞችና ተቋማት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ኢንዱስትሪው በአሁኑ ወቅት የተለያየ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ከ3 ሺሕ 400 በላይ ትራክተሮች፣ 318 የውሃ ፓምፖች እንዲሁም ሌሎች የግብርና ማሽነሪዎችን ለማምረት የሚያስችል ጥሬ እቃ እንዳለው የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢያሱ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡

ሔብሮን ዋልታው (ከአዳማ)