የኢትዮ-ኬንያ ሁለትዮሽ ውይይት

የኢትዮ-ኬንያ ሁለትዮሽ ውይይት

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ራይሸል ኦማሞ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

ኬንያ እና ኢትዮጵያ የቆየ ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሰረተ ልማት ትስስርም ጭምር የበለጠ ግንኙነታቸውን እያሳደጉ ነው፡፡

ረፋዱን አዲስ አበባ የገቡት ሚኒስትሯ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንሚመክሩ ነው የተጠቆመው፡፡ ሚኒስትሯ ግንቦት 30/2013 በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝትና ምክክር አድርገው መመለሳቸውም የሚታወስ ነው፡፡

(በሰለሞን በየነ)