የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጎንደር ገቡ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋምት ጉባኤ አመራሮች በጎንደር ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማፅናናት ጎንደር ከተማ ገቡ።

የጉባኤው አመራሮች የሰባት ቤተ እምነት ተወካዮችን ያካተተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተጎዱ ወገኖችን ተዘዋውረው በመመልከት እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል።

ነገ ደግሞ ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገልጸዋል።

የጉባኤው አመራር አባላትን በአፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘትም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጎንደር ከተማ ሰላምና ልማት ሸንጎ አባላት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።