የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማላዊ ገባ

ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) ዛሬ ረፋዱ ላይ ከአዲስ አበባ የተነሳው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በማላዊ ሊሎንግዌ ካሙዙ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሠላም ደርሷል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ማረፊያውን ሰን በርድ ሆቴል ያደረገ ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ እና ግብፅ ጋር የሚጫወት መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡