የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ በረራ ጀመረ

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ተከትሎ አቋርጦት የነበረውን የላሊበላ በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

ወራሪውና አሸባሪው ቡድን በወገን ጦር ከባድ ምት ተቀጥቅጦ አካባቢውን ሲለቅ በላሊበላ አየር ማረፊያን ውደመትና ዘረፋ ማድረሱን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘረፋና ውድመት የደረሰበትን የላሊበላ አየር ማረፊያ በአፋጣኝ አስተካክሎ ወደ ሥራ እንዲመለስ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር።

የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም ለማነቃቃት እና በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የሚከበረውን ታላቁን የገና በዓል ለማክበር መንግሥት በወሰደው እርምጃ አየር መንገዱ በአፋጣኝ ተጠግኖ ለአገልግሎት ብቁ ኾኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም አቋርጦት የነበረውን በረራ ዳግም ጀምሯል።

አየር መንገዱ የልደት በዓልን በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ለሚያከብሩ ምዕምናንና አካባቢውን ለሚጎበኙ ጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሚኮ ዘግቧል።