የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ አቋርጦት የነበረውን በረራ በይፋ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት አቋርጦት የነበረውን በረራ  በይፋ ጀምሯል።

አየር መንገዱ በትግራይ ክልል በህወሃት ጁንታ ላይ ይወሰድ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በረራውን አቋርጦ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ የህግ ማስከበሩ ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላ ትላንት ምሽት ከአዲስ አበባ መንገደኞችን ጭኖ የመጀመሪያ በረራውን በማድረግ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤር ፖርት ደርሷል።

በኤርፖርት ለደረሱት መንገደኞችም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል ጀነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተባባሪ አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚአብሔር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መቀሌ የደረሰው አውሮፕላን ሌሎች መንገደኞችን አሳፍሮ ምሽቱን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ታውቋል።

የኤርፖርቱ ሰራተኞችም በሙሉ በስራ ገበታቸው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በቀጣይ አየር መንገዱ በቀን ሁለት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ይቀጥላል በመባሉን ኢዜአ ዘግቧል።