የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ።
እንዲሁም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በቅርቡ አዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደሚያሳውቅም ገልጿል፡፡