የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎችን እያስመረቀ ነው

ሰኔ 18/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል “ነብሮች 2014” በሚል መሪ ቃል ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል።
ተመራቂ አብራሪዎቹ በተለያዩ አውሮፕላን አይነቶች በጀማሪነት እና ተጨማሪ አብራሪነት ስልጠና የወሰዱ ነባር እንደሆኑ ተገልጿል።
በአየር ኃይል አካዳሚ ለ4 ዓመታት ያህል ስልጠና ተከታትለዋል።
ተመራቂዎቹ መካከልም በተዋጊ አውሮፕላን ፣ በትራንስፖርት አውሮፕላን፣ በትራንስፖርት ሂሎኮፕተር፣ ቪ አይፒ ሂሎኮፕተር እንዲሁም በመጀመሪያ ደረጃ በረራ ማሰልጠኛ አውሮፕላን አብራሪነት የሰለጠኑ ናቸው።
የአየር ኃይል አካዳሚ የጀግኖች አብራሪዎችና የብቁ ቴክኒሻኖች ማፍሪያ ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል አቅም የሚፈጥረት ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የአየር ኃይል ዋና መምሪያ አዛዥ ይልማ መርዳሳ ፣ ሚኒስትሮች ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ፣ ጄነራሎች እንዲሁም የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ታድመውታል።
በሰለሞን በየነ