“የኢትዮጵያ እና የዜጎቿ የአሸናፊነት ምስጢር ከአባቶቻችን የወረስነው አንድነትና ቁርጠኝነት ነው” – ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) “የኢትዮጵያ እና የዜጎቿ የአሸናፊነት ምስጢር ከአባቶቻችን የወረስነው አንድነት እና ቁርጠኝነት ነው” ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቶችን ድል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ የአሸናፊነትን ተምሳሌት ለዓለም ሕዝብ ላሳዩት የኢትዮጵያ አትሌቶች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ለተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ተጋልጣለች፤ ነገር ግን ዜጎቿ አንድም ጊዜ ለእነዚህ ችግሮች እጅ ሳይሰጡ በአንድነት እና በጀግንነት ድል እያስመዘገቡ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ሀገር ማስቀጠል ችለዋል” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ዛሬም እንደ አባቶቻቸው በሁሉም የትግል ሜዳዎች ድል እያመስዘገቡ ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር እያሳዩ ነው፣ ጀግኖች አትሌቶቻችን በዓለም ሻምፒዮና ላይ ድንቅ ድል በማስመዝገብ አኩርተውናል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።