የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ/ቤ/ን መልዕክት

ጳጉሜ 3/2013 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን የ2014 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትን አስተላለፈች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያዊያን፣ በአገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ፣ ለሀገራችሁ ሉኣላዊነት ድንበር እያስጠበቃችሁ ያላችሁ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2014 አደረሳችሁ” ብለዋል።

ብፁዕነታቸው በምንገኝበት 2014 መግቢያ ላይ ቆም ብለን ማሰብ አለብን ያሉም ሲሆን፤  በአሮጌው ዓመት ያልሰራናቸውን በጎ ሥራዎች በአዲሱ 2014 ለመስራት ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን መትጋት አለብን ነው ያሉት::

በሜሮን መስፍን