ሰኔ 17/2013 (ዋልታ) – የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት 72ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
በይነ መረብ የሚካሄደው በዚህ ስብሰባ በደቡብ ሱዳን፣ በሶማሊያ፣ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ የሚያተኩር ነው፡፡
በስብሰባው የኢጋድ አባል አገራት የስደተኞች ፖሊሲ እና በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ላላው የዜጎች መፈናቀል ዘላቂ ስትራቴጂካዊ መፍትሄዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡