የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለ64 አባላት የማዕረግ ሹመት ሰጠ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

ሚያዝያ 09/2013 (ዋልታ) – በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለ64 አባላት የማዕረግ ሹመት ሰጠ፡፡

ተሸላሚ አባላቱ በመልካም የስራ ውጤት የላቀ አፈፃፀም ያመጡ የባለ ሌላ ማዕረግተኞች፣ መስመራዊ መኮንኖች እና ከፍተኛ መኮንኖች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተሸላሚዎቹ ቤተሰቦቻቸውና ከፍተኛ አዛዦች በተገኙበት የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት ተደርጓል፡፡

በመከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ በመከላከያ ሰራዊቱ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች አመርቂ ውጤቶች እያመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለተሿሚዎች ማዕረግ ያሰጡት በኢፌዲሪ መከላከያ የሰራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ፣ የላቀ ውጤት በማምጣት ለሽልማት የበቁትን በማመስገን በቀጣይም ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡