የኢፌዴሪ መከላከያ ያሰለጠናቸው ወታደሮች ዛሬ ያስመርቃል

የኢፌዴሪ መከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመመልመል ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ምልምል ወታደሮቾ በዛሬው ዕለት ያስመርቃል።

ሰራዊቱን የተቀላቀሉ እና መስፈርቱን ያሟሉ ተመራቂ ምልምል ወታደሮች፣ ሁርሶ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው በየማሰልጠኛ ማዕከሉ ይመረቃሉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትም ለተመራቂ ምልምል ወታደሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡