የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

                                                       የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ጥር 26/2014 (ዋልታ) የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ፈይሰል አልይ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።