የእነ አንባቸው መኮንን 3ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ በደም ልገሳ ታሰበ

ሰኔ 18/2014 (ዋልታ) ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በሥራ ላይ እያሉ የተገደሉት የቀድሞ የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አንባቸው መኮንን (ዶ/ር) ፣ የርዕሠ መስተዳድሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኃላፊ ምግባሩ ከበደ የ3ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ አዲስ አበባ በሚገኘው የደም ባንክ ደም በመለገስ ታስቧል።
የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓቱ “ከራስ በላይ ለሀገር ታሪክ ይነገር” በሚል መሪ ሀሳብ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችና ወደጅ ዘመዶቿቸው በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በምንይሉ ደስይበለው