የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ አካባቢ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ጎንደር በመገኘት የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት ለዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም እና በተመድ የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ ያደረገውን የ10 ሚሊየን ፓውንድ የሰብዓዊ ድጋፍ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንግሊዝ በትምህርቱ ዘርፍ ድጋፍ ከምታደርግባቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በምስራቅ ጮራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ትናንት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡