የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ቀን በአዳማ ከተማ እየተከበረ ነው

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ቀን ለ3ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ አማካኝነት በአዳማ ከተማ እየተከበረ ነው።

የኅብረት ስራ ማህበራት “ለዘላቂ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት” በሚል መሪ እየተከበረ ሲሆን  የፌዴራል እና የክልል የማኅበራቱ አመራሮች እንዲሁም ከፍተኛ የኦሮሚያ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ አንድ መቶ ሞዴል አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ሲሆን ባለ አክስዮኖችም መታደማቸው ታውቋል፡፡

በነገው እለትም የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ 17ኛ ዙር ጉባኤን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በቡላ ነዲ (ከአዳማ)