የኦሮሚያ የባህል ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 18/2014 (ዋልታ) “ባህላችን ለቱሪዝም ዕድገታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የባህል ሳምንት (ፌስቲቫል) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡
ፌስቲቫሉ ዛሬ ጠዋት በጎዳና ላይ ትርዒት መከበር ጀምሯል፡፡
ከክልሉ በተጨማሪ የሌሎች ክልሎች የባህል ቡድን አባላት በተጋባዥነት በባህል ሳምንቱ እየተሳተፉ ነው፡፡
በባህል ሳምንቱ ላይ ሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የባህል ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በጎዳና ላይ ትርዒት፣ የባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች አውደርዕይ፣ በተለያዩ ሙዚቃ ባንዶች መካከል ውድድር ይቀርብበታል ተብሎ ይበቃል፡፡
የፓናል ውይይት እንዲሁም የጥናትና ምርምር ሲፖዚየምም የባህል ሳምንቱ አካል እንደሚሆን እንደሚሆን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።
ለኦሮሞ ባህልና ኪነጥበብ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅናና ምስጋና የሚሰጥም ይሆናል፡፡