የከተማ አስተዳደሩ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በመታወቂያ አሰጣጥ ሂደት ላይ ተወያየ

ቀንአ ያዴታ (ዶ/ር)

ኅዳር 8/2014 (ዋልታ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ውይይት አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቀንአ ያዴታ (ዶ/ር) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

መመሪያው ሰላማዊ እና ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመለየት፣ የሐሰት መታወቂያ የሚሰጡ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ለመለየት እንዲሁም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሆነው ያለ አግባብ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጡትን ለመቆጣጠር ያግዛል ብለዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል ያሉት ኃላፊው ከህዳር 6 /2014 እስከ ህዳር 15/2014 በሚቆየው የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ሂደት ማህበረሰቡ መታወቂያ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

የሎጂስቲክ እና የሰው ኃይል ቅድመ ዝግጅት ተካሂዶ አርብ ህዳር 10/2017 በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ መታወቂያ ለማህበረሰቡ ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል።

በቁምነገር አሕመድ