የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለመከላከያ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ በጋራ ያዘጋጁት መርሀ ግብር በ ብሄራዊ ትያትር እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በጋራ ያዘጋጁት መርሀ ግብር በ ብሄራዊ ትያትር እየተካሄደ ነው።
መከላከያ ሰራዊት እና ኪነ ጥበብ ታሪካዊ ትስስር አላቸው ያሉት በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ፣ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይወናበድ፣በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ እንዳይሸበር ብሎም መቼም ፣የትም እና በምንም መልኩ የሀገር ፍቅሩን እንዲያስቀድም ኪነ ጥበብ የበኩሏን አስተዋፅኦ ልታደርግ ይገባል ብለዋል።
ባለፋት በርካታ አመታት ኪነ ጥበብ ሀገር በችግር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ ሁሉ ከህዝብ ጎን ቀመሆን ከጎን መቆሟ ይታወሳል።
በዛሬው ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በጋራ ያዘጋጁት መርሀ ግብር ላይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ብርጋዴል ጄነራል ተስፋዬ፣ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሰርከስ ትርኢቶች፣አገራዊ ሙዚቃዎች ፣የግጥም ስራዎች እና መዝሙሮች እየቀረቡ ይገኛሉ።