የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በውትድርና ማሰልጠኛ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) – የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፤ መቼም የትም በምንም” ለሚለው አገራዊ ጥሪ መልስ ለመስጠት በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ለሚገኙ ሰልጣኞች የመድረክ ስራዎችን እያቀረቡ ነው፡፡
ባለሙያዎቹ የአገር ፍቅር፣ ራስ ቴአትር፣ ከህጻናትና ወጣቶች ቴአትር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ባህል አዳራሽ የተውጣጡ ናቸው።
በመድረኩ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ አመራሮችና የተለያዩ የመከላከያ ሰራዊት መስመራዊ መኮንኖች መገኘታቸውን ኢፕድ ነው የዘገበው።