የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች መከበር ጀምሯል

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል (ማሽቃሬ ባሮ) በዞኑ ዋና ከተማ ቦንጋ እና ወረዳዎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የብሔሩን ታሪክ፣ ባህልና ትውፊት የሚያሳይ ኤግዝብሽንና ፈስቲቫል እየተካሄደ እንደሚገኝ የካፋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ምራዕብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ  ፀጋዬ ማሞ እና የክልlu ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብር ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎችም የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በዞኑ ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡