የኬንያ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረጉ ነው

ነሀሴ 22/2013 (ዋልታ) –  የኬንያ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች በአዲስ አበባ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል፡፡በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የሁለትዮሸ ግንኙነት ለማጠናከር በተለይም በንግድ እና በኢንቨስትመን ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ ከኬንያ የመጡ የጉዞ ወኪሎች ፣ የኬኒያ የቱሪዝም መዳረሻ አስጎብኚዎች አንድነት ፓርክ ፣ እንጦጦን ፓርክ እንዲሁም በብሄራዊ ሙዝየምን የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

በቀጣይም በኢትዮጰያ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መደረሻ ቦታዎችን እንደሚጎበኙ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስተውቋል።
(በሜሮን መስፍን)