የኬንያ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

ነሀሴ 22/2013 (ዋልታ) – የተለያዩ የኬንያ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ የጉዞ ወኪሎች፣ የሳፋሪ ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ይጎበኛሉ።
እነዚህ አስጎበኚዎች እና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ እና ለቱሪስቶች በመሸጥ እንዲሁም የኢትዮጵያ በጎ ገፅታ ለኬንያ እና ለሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉብኝቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተባባሪዎች በጋራ በመተባበር ያዘጋጁ መሆኑን በኬኒያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።