የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ የሀረሪ ክልል ጥሪ አቀረበ

ሚያዚያ 10/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በመላው አለም የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡና ከኢድ እስከ ኢድ እና የሸዋል ኢድ በዓላት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

መንግስት በውጪ ሀገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፈውን ጥሪ ተከትሎ “ከኢድ እስከ ኢድ” መረኃ ግብርን ጨምሮ በክልሉ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የሸዋል ኢድ በዓልን የተሳካ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በመሆኑም በክልሉ በተለይም የሸዋል ኢድ በዓልን ከወትሮው በተለየ መልኩ ለማክበር የተለያዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ኩነቶች እንደሚከናወኑ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።

ከዚህ ባሻገርም በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚሰማሩ ዲያስፖራዎች ምቹ ሁኔታ ለማፍጠር በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል።