የክልሉ የመንግሥት የልማት ድርጅት እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ

መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት “የቤጉ ዴቨሎፕመንት ግሩፕ” (BG Developoment Group) የተሰኘ የመንግሥት የልማት ድርጅት እንዲቋቋም በቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በጉዳዩ ላይ በስፋት የተወያየው የመስተዳድር ምክር ቤት “የቤጉ ዴቨሎፕመንት ግሩፕ” በኮንስትራክሽን፣ ማዕድን፣ ግብርናና ጥናት ዲዛይን ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አስታውቋል።

በዚህም በክልሉ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት በራሱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመጣመር የክልሉን ልማት ለማፋጠን አንደሚሰራ ተጠቁሟል።

የሚቋቋመው ድርጅት በክልሉ የሚነሱ የልማት ክፍተቶችን እና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ታምኖበት በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።