የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነስርዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በቅድስተ ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ።

በ1928 በሰሜን ሸዋ ምዕራብ ጃርሶ ወረዳ የተወለዱት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና 1972 መስከረም 17 ግሸን ማርያምን ለመሳለም በሄዱበት አጋጣሚ ነበር ዛሬ ለበርካቶች እናት ይሆኑ ዘንድ አዲስ ምዕራፍን የከፈቱት።

ላለፋት 41 አመታት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ህፃናትን አሳድገው ለታላቅ ቁምነገር አብቅተዋል።

ክብርት አበበች ጎበና እናቶችን በሙያ በማሰልጠን ሴቶች ድህነትን አሸንፈው የተስተካከለ ህይወት እንዲኖሩ አድርገዋል።

የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና አበበች ጎበና በኮቪድ-19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በ85 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

(በቁምነገር አህመድ)