በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት በመጪዎቹ መጋቢትና ሚያዚያ ወራት ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ከአለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች ክትባት አምራች ኩባንያዎች ጋር በመሆን ክትባቱን 20 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ መሆኑን ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡
ለጤና ባለሙያዎች፣ ለማህበረሰብ አገልግሎት ሰራተኞች፣ ለመምህራን እንዲሁም ለአረጋውያንና ተጎዳኝ በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች ክትባቱ በቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
በተያያዘም ሚነስትሯ ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎትን ያድርጉ›› የሚለው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፣ ሁሉም ህብረተሰብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየተስፋፋ መሆኑን በመገንዘብ በአለም ጤና ድርጅት የተገጹ መከላከያ መንገዶችን መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
(በሳራ ስዩም)