የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተገለጸ

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

ነሐሴ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ የ2016 አፈፃፀም እውቅና አሰጣጥ መርኃ ግብር ተካሂዷል።

የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ሀገር የጣለችበትን አደራ በብቃት ለመወጣት በተለይ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ውጤታማ ስራ ሰርቷል ብለዋል።

መምሪያው በ2016 በጀት ዓመት 7 ሺሕ ላይ መዝገቦችን በመመርመር ከ300 ሺሕ በላይ የፎረንሲክ ምርመራ በማድረግ ስኬታማ ስራ መስራቱንም አብራርተዋል።

በመርኃ ግብሰሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የስራ የኃላፊዎች እና የፖሊስ ሰራዊት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሳራ ስዩም