የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

ነሐሴ 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው እለት በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተክለዋል።

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር “የምትተክል ሀገር፤ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ሲሆን ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በሁሉም መርኃ ግብሮች የራሱን አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የኮርፖሬቱ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ እምርታ አስፋው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ ዋልታ ግቢን ጨምሮ በአካባቢው ባሉ ወረዳዎችና ትምህርት ቤቶች በሚዲያው አስተባባሪነት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች መከናወናቸውንም ተናግረዋል።

ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መንከባከብ ላይ እንደሚሰራና ለዚህ ሲባልም ሰራተኞች ተቀጥረው እንዲከታተሉ መደረጉን አንስተዋል፡፡

ምክትል ሥራ አስፈጻሚዋ ሀገርን ማልማት ጥቅሙ ለራስ በመሆኑ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሁሉም ሰው በጋራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡