ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – ዋልታ ቴሌቪዥን አመራሮችና ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቦሌ ክፍለ ከተማ በጋራ በመሆን ከሶስት ሺህ በላይ ችግኞችን በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በጫንጮ ከተማ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፓርክ ተክለዋል፡፡
የተተከሉ ችግኞችን በየስድስት ወሩ የተቋማቱ ሰራተኞች በስፍራው በመገኘት እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸው ተገልጿል።
በወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ከችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በተጓዳኝ በጫንጮ ከተማ የሶስት አቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እንደሚደረግም ተመላክቷል።
ለችግኝ ተከላውና ለቤት እድሳቱ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገም ተነግሯል፡፡
ተቋማት አንድላይ በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ መሠረት ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማድረግ ያለመ መርሀ ግብር እንደሆነም ተገልጿል።
በተጨማሪም በተቋማቶች መካከል ያለውን በጋራ የመስራት መንፈስ ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተጠቁማል።
የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎችም ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር እንደ ህዝብ እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀማቸው አስተማሪነቱ የጎላ መሆኑን የዋልታ ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
በችግኝ ተከላው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ፣ የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬ ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ ነዋሪዎች ፣ ወጣቶና ሴቶች እና የጫንጮ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
(በዙፋን አምባቸው)