የዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የአረብ ኤመሬትስ ዓለም ዐቀፍ ቀይ ጨረቃ ማኅበር ዋና ፀኃፊ ፉአድ አብዱርህማን በሮቤ የተገነባውን የዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መረቁ።

ትምህርት ቤቱ በማኅበሩ ድጋፍ በባሌ ዞን ውስጥ ከተገነቡ መሠረተ ልማቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጭ የተደረገበት ነው።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአንድ ዓመት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ24 በላይ የመማሪያ ክፍል እና ከ1 ሺሕ 200 በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው።

ሚልኪያስ አዱኛ (ከሮቤ)