የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በአጭር፣ መካከለኛና ረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው ወደ ሥራ መገባቱን መንግሥት ገለጸ

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

መጋቢት 24/2014 (ዋልታ) የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በአጭር፣ መካከለኛና ረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው ወደ ሥራ መገባቱን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የኢኮኖሚ መረጋጋትና የኑሮ ውድነት፣ የሰብኣዊ እርዳታ ማጓጓዝ እንዲሁም የሰላምና ደኅነንት ጉዳይ ላይ ትኩቱን አድርገዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ድህረ ጉባኤ ከማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት በስፋት የተነሳው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ችግሩን ለመፍታት መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ የሚያወሩበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የዋጋ ንረትን ለማባባስ የሚሰሩ ህገወጥ እንቅስቃሴ ለመከላከል የፀጥታና የፍትህ ተቋማት ያሉበት ግብር ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በተጠናቀቀው ሳምንትም ህገወጥ ክምችት የፈፀሙ ስምንት የነዳጅ ማከማቻዎችና 25 መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ የደበቁ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ዜጎች ከቀያቸው ሳይፈናቀሉ ባሉበት እርዳታ እንዲያገኙ መንግሥት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአየር ትራንስፖርት በየቀኑ የሰብኣዊ እርዳት የሚያቀርቡ ተቋማት በሚችሉት ደረጃ እያቀረቡ መሆናቸውን የተናገሩት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)  በየብስ ደግሞ በዓለም የምግብ ፕሮግራም አማካኝነት 20 ተሳቢ መኪኖች ተንቀሳቅሰዋል ብለዋል፡፡ ከነዚህም በትናንትናው ዕለት 13 የሚሆኑት መቐሌ ደረሰዋል፤ ቀሪዎች ደግሞ ዛሬ ይገባሉ ሲሉም አክለዋል፡፡

ሆኖም ግን የታጣቂ ኃይሎች ደጋፊዎች የሀሰት መረጃ እያሰራጩ መሆናቸውን ጠቁመው ተድሮስ አድሀኖም ይህንን  የሀሰት መረጃ በቲውተር ገጹ እያሰራጨ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ የሰብኣዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተተቁሟል፡፡

በሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ሽብርተኛው ሸኔ የሚያደርሰውን ጅምላ ግድያ ጥቃት ለማስቆም ኦፕሬሽን እየተካሄ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በተለያዩ ቦታዎች እየተደመሰሰ ያሉት ሚኒስትሩ በሽብር ቡድኑ ተታለው የገቡ ወጣቶችም በአባ ገዳዎች አማካኝነት ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

 

በምንይሉ ደስይበለው

 

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!