የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በምርምር መደገፍ እንደሚገባ ተጠቆመ

ሰኔ 3/2014 (ዋልታ) የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በጥናትና ምርምር የተደገፈ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብቷን በአግባቡ ያለመጠቀሟ ምክንያት የውሃ ኃይል አጠቃቀም በምርምር የታገዘ ባለመሆኑ ነው ተብሏል።

20ኛው ዓለም ዐቀፍ ዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት ሲምፖዚየም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የውሃ ሀብትን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይልን ማጠናከር በሚቻልበት እንዲሁም በውሃ ሀብት የመስኖ እርሻን ማጠናከር እና መሰል ጉዳዮች ላይ የተሠሩ ምርምሮች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)ን ጨምሮ በርካታ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ዙፋን አምባቸው (ከአርባ ምንጭ)