የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በባሕርዳር እየተካሄደ ነው

የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን የሚያወግዝ ሰልፍ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን እያካሄዱት ባለው ሰልፍ ምእራባዊያን በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ እያደረሱ ያለውን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ድምጽ እየተስተጋባ ነው።

ሰልፈኞቹ ቢቢሲና ሲ ኤን ኤን የሐሰት መረጃ ማስተላለፍ ያቁሙ፣ በሐሰት መረጃ የሚፈርስ ሃገር የለም፣  ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅምና ግድቡ ተሞልቷል” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ናቸው።

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ አሜሪካ በዴሞክራሲ ስም መነገድ ታቁም ‘no more’ ”በቃ” የሚሉ መፈክሮችም በሰልፈኞቹ እየተስተጋቡ መሆናቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።