የካቲት 22/2014 (ዋልታ) 126ኛው ዓመት የዓድዋ ድል በተለያየ ሁነቶች እየታሰበ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ዓድዋን በሚዘክሩ የተለያዩ መርሃ ግብሮች እየታሰበ ይገኛል።
ዓድዋ “የኢትዮጵያዊያን ህብረት ፣ የአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል መሪ ቃል ከከተማ አስተደደሩ ከተወከሉ ወጣቶች ጋር የፓናል ዉይይት እየተደረገም ይገኛል።
በመርኃ ግብሩ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች፣ አባት አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በሰለሞን በየነ