የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችን መረጠ

ወንድሙ ኩርታ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) አዲሱ 11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ መረጠ፡፡

በዚህም ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል፡፡

አቶ ወንድሙ ኩርታ የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ጽህፈት ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተጠቁሟል፡፡

ወ/ሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፌ ጉባኤ በመሆን መሾማቸው ተመላክቷል፡፡

ወ/ሮ ገነት መንገሻ

ወ/ሮ ገነት መንገሻ በዳውሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዘርፍ ኃላፊ ሆነው ማገልገላቸውም ተገልጿል።

የክልሉ ምክር ቤት ሹመታቸውን በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ቃለ መሀላም ፈጽመዋል።