የደቡብ ክልል መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ66 ሚሊየን በላይ ብር የሚገመት የስንቅ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ 40 ሚሊየን በገንዘብ 26 ነጥብ 9 ሚሊየን ደግሞ በአይነት ነው ተብሏል።

ድጋፋን ለመከላከያ ሚኒስቴር ያስረከቡት የደቡብ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ ተፈሪ አባተ አሸባሪው ቡድን እስኪደመሰሰ የክልሉ ህዝብ በሁሉም መልኩ ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ድኤታ ማርታ ሊዌጅ የክልሉ ህዝብና መንግስት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆማቸው አመስግነው ሁሉም የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

(በህይወት አክሊሉ)