የደቡብ ክልል ም/ቤት አባላት የጥቅምት 24 ጥቃትን አሰቡ

ጥቅምት 24/2014 (ዋልታ) – የደቡብ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ የህሊና ፀሎት አድርገዋል፡፡
አባላቱ በቅርቡ የከሃዲው ጁንታ የመጨረሻ የቀብር ሥርዓት እንደሚፈፀም ተናግረዋል።
የተጀመረው የህልውና ዘመቻ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ መደበኛው ህይወት ለመመለስ ሁሉም ዜጋ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን የደቡብ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡