የደቡብ ክልል ምክር ቤት 2 ሹመቶች አጸደቀ

መጋቢት 10/2014 (ዋልታ) መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የቀረቡለትን 2 ሹመቶች በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በዚህም ምክር ቤቱ ክፍሌ ዋናን የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሲሾም አበራ ኪፔን ደግሞ የክልሉ ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንዲያገለግሉ ሾሟል፡፡

ተሿሚዎቹ ከወረዳ ጀምሮ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ላይ የሰሩና ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።