የደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱን ገለጸ

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሳሙኤል ቀቀቦ በ4ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 610 ሚሊየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ 548 ሚሊየን ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

እንደ ክልል 103 ሺሕ 733 ሄክታር ለተከላ ልየታ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

ሀገር በቀል የደን ዝርያ እና ቀርካሃ ላይ እየሰራ ሲሆን በ5 ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ 4 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ የቆላና የደጋ ቀርከሃ ዝግጁ ሆኖ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

በክልሉ የብዝኃ ህይወትን ሀብትና ልማት መጠበቅና እየተመናመኑ የመጡ የእፅዋት ዝርያዎችን ማብዛት እና መልሰው እንዲያገግሙ ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶታል ሲሉም ጠቁመዋል።

ሐምሌ 15/2014 ዓ.ም ኅብረተሰቡም አረንጎዴ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።