የደቡብ ወሎ ዞን የዘመቻ ህልውና የክተት ጥሪ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

ሐምሌ 20/2013(ዋልታ) – የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘው ተሻገር የክተት አዋጅ ጥሪን ተከትሎ የደቡብ ወሎ ዞን የዘመቻ ህልውና የክተት ጥሪ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማዳን ወሎ ላይ የሚደረገው ትግል ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው አሁን የምንገኝበት ወቅት ዓለም አቀፍ ድል የተቀዳጀንበት በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራችንን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት ለመጠበቅ የተዘጋጀንበት ነው ብለዋል፡፡

የሥራ ኀላፊዎች ራሳቸውን የማዘጋጀት፣ ኅብረተሰቡን የማደራጀት እና የማንቃት ሥራ መሥራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበት በአሁኑ ወቅት ማኅበረሰቡ አሁን የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ እንዲዘምትም ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበትን ጨምሮ የፌዴራል የክልል እና የዞኑ የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡