የዳግማዊ ምኒሊክ ሪፌራል ሆስፒታል ዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ተጠናቀቀ

ጥር 20/2014 (ዋልታ) በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፌራል ሆስፒታል ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባው የዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

ማዕከሉ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ነው የተባለው፡፡

30 የዳያሊሲስ ማሽኖች የሚኖሩት ማዕከሉ የህፃናት ማቆያ ክፍል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የቀዶ ጥገና ክፍል፣ የሀኪሞች ክፍል፣ የታማሚዎች ክፍል፣ ለይቶ ማቆያ ክፍል እንዲሁም ሀኪሞች ታካሚዎቻቸውን በቅርበት የሚከታተሉበት ነርስ ስቴሽን እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ለ30 ታካሚዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለውና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ማዕከሉ አሁን ላይ የግንባታ ሥራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡