መስከረም 14/2015 (ዋልታ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ14ኛ ጊዜ የሕክምና ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ700 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሁሴን ቃሲም (ፒኤችዲ) እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በሽር አብዱላሂን (ፒኤችዲ) ጨምሮ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 704 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል 428ቱ በሕክምና ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ የተማሩ ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
የተቀሩት በትምህርት አመራር፣ በትምህርት ማኔጅመንት፣ በሶሺዮሎጂ፣ በማኔጅመንትና አካውንቲንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉና የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች እንደሆኑ ተገልጿል።