የገቢዎች ሚኒስቴር በ8 ወራት ከ221 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስምንት ወራት 221 ቢሊየን ከ487 ሚሊየን 562 ሺሕ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሚኒስቴሩ የዕቅዱን 92 ነጥብ 16 በመቶ መፈፀም መቻሉን አስፍረዋል፡፡

ውጤቱ ግብር ከፋዮች በወቅቱ በመክፈላቸው፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው እንዲሁም በአጋር አካላትና የሕዝብ ድጋፍ የተገኘ ነው ብለዋል፡፡