የገንዘብ ሚኒስትሩ ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) ከዓለም ባንክ እና ከአይኤምኤፍ ጉባኤ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር በአሜሪካ ተወያዩ።

በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ መንግስት ባካሄዳቸው የኢኮኖሚ የሪፎርም ስራዎች፣ ስለ ሰላም ሂደቱ፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም ሪፎርሙን ለመተግበር እና ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ለመፍታት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ሀገራት እና የልማት አጋሮች ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው መንግስት እያደረገ ያለውን ሪፎርም እንደሚያደንቁ መግለፃቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል።

አያይዘውም የሰላም ሂደቱን እንደሚደግፉ በመጥቀስ ብሪታንያ ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!