የጋራ ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

ሚያዝያ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ራሄል ባፌ (ዶ/ር) የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገሪቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም ቅድሚያ ለሰላም በመስጠት እየሄዱበት ያለውን መንገድ አድንቀዋል።

6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በሰላም የተጠናቀቀውም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅድሚያ ለአገር ሰላም በመስጠታቸው ነው ብለዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ዓመታዊ የሥራ ክንውን ሪፖርት እያዳመጠ ነው።

ምክር ቤቱ በአገራዊ ምክክሩ ዙሪያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

በመስከረም ቸርነት