የጎንደር ባለሃብቶች ለኅልውና ዘመቻው ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለፁ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) የጎንደር ከተማ ባለብቶች ሰርቶ መኖር የሚቻለው አገር ሲኖር በመሆኑ የጀመርነውን የኅልውና ዘመቻ ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን አሉ።
‹‹ህይወታችንና ገንዘባችንን ለኅልውናችን›› በሚል መሪ መልዕክት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በኅልውና ዘመቻ ዙሪያ ከከተማው ባለሀብቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱ የተገኙት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ የአማራን ሕዝብ ለማዋረድ የመጣውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ እየተደረገ ያለውን የኅልውና ትግል በመደገፍ የጎንደር ባለሀብቶች እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚመሰገን ነው ብለዋል።
አሁንም ወራሪውን ኃይል እስኪደመሰስ ሁሉም የከተማው ባለሀብትና ነዋሪዎች ደጀን የመሆን፣ የመዝመትና አካባቢን ከሰርጎ ገቦች የመጠበቅ ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የህይወት መስዋእትነት እየከፈሉ ለሚገኙ አገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ እንዲሁም የዘማች ቤተሰቦች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።
በጎንደር ከተማ ለኅልውና ዘመቻው 69 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቡን አሚኮ ዘግቧል፡፡