የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

ኅዳር 3/2014 (ዋልታ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ።

በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በዞኑ ጀጃ ባህሪ ግንብ ቀበሌ የዘማች ቤተሰቦችን የደረሱ ሰብሎች የመሰብሰብ ሥራ በማከናወን ደጀንነታቸውን ማስመስከራቸውን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሳሁን ተገኘ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲው የግብርና ኮሌጅ የተፈጥሮ ሃብት ትምህርት ክፍል መምህርና የመርሃግብሩ አስተባባሪ መምህር ፍቃዱ ሀብቴ ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።