የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢዎች የችግን ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ

የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢ ጋዜጠኞች በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሂደዋል።

በመርኃግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩምና የሴክሬታሪያቱ ባልደረቦች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች የተሳተፉ ሲሆን የተተከሉት ችግኞች ሀገር በቀል ዕፅዋት መሆናቸው ተጠቁሟል።

በወቅቱ ንግግር ያደረጉት ቢልለኔ ስዩም ኢትዮጵያዊያን በምግብ ራስን ለመቻል እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አረንጓዴ አሻራን አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።

መገናኛ ብዙኃኑም የራሳቸውን አሻራ በማሳረፍና ችግኝ ተከላውን እስከ ክትትል ድረስ በመዘገብ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

4ኛው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻር መርኃግብር “አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ መልዕክት ከሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን እስከ ትናንት ድረስ ከ3 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን ተናግረዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW